የአፋር ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጅግጅጋ ከተማ በመገኘት ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አስረክበዋል።
የአፋር እና የሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች በተለያየ ጊዜ እርስ በእርስ ሲደጋገፉ የመጡ መሆኑ በዚህ ወቅት ተገልጿል፡፡
የአፋር ክልል በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ወረራ ከፍተኛ የሆነ ችግር ውስጥ ቢሆንም ለወንድም ሶማሌ ህዝብ በድርቅ ምክንያት ለደረሰበት ጉዳት የክልሉ መንግስት ድጋፉን አድርጓል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፥ የአፋር ክልል በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።