Fana: At a Speed of Life!

የኢኮኖሚና የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ጥያቄዎች እንዲፈቱ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በትኩረት ይሰራል – ወጣት አክሊሉ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ መድረክ በአዳማ መካሄድ መጀመሩን የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በፓርቲው የወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝደንትና የጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አክሊሉ ታደሰ የውይይት መድረኩ በሶስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የጉባኤ ውሳኔዎችን አስመልክቶ የወጣቶች መድረክ አፈፃፀም መገምገም፣ የምግቤን ከጓሮዬ የደረሰበትን ደረጃ መገምገም እንዲሁም በቅርቡ ለሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ 1ኛ ጉባዔን በተመለከተ የውይይት መነሻ አጀንዳዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ኃላፊው አያይዞም ፥ በፓርቲው ጉባኤ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎች ዙሪያ ማወያየት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ከ3 ሚሊየን በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ ሀገራዊ መድረክ ሃገራችን አሁን ባለችበት ዘርፈ ብዙ ጫናዎች ውስጥ ባለችበት የተካሄደ መድረክ በመሆኑ በሁሉም ክልሎች ወጣቱ ያለውን ጥያቄ በሚገባ ለመረዳት ያስቻለ ነበርም ብለዋል፡፡

በፓርቲው ውሳኔዎች ላይ ወጣቶች በራሳቸው አደረጃጀት ውይይት ማድረጋቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ወጣት አክሊሉ ፥ ወጣቶቹ በስፋት መፈታት አለባቸው ብለው ያነሷቸውን የኢኮኖሚ ጥያቄዎች፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና መሰል ጥያቄዎች እንዲፈቱ የሊጉ መዋቅር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የወጣት ሊጉ ስራ አስፈጻሚ አባላት የወጣቶች የውይይት መድረክን ለመምራት በየተመደቡበት ክልል የነበረውን ጠንካራና መስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.