Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ከቀናት በኋላ በዩጋንዳ አስተናጋጅንት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የሴካፋ ሴቶች እግርኳስ ውድድር ላይ ሉሲዎቹ በአሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የሚመሩ ይሆናል፡፡

አሰልጣኝ ፍሬው ከ20 ዓመት በታች የሴቶቹን ብሔራዊ ቡድን ይዞ በሴካፋ ዋንጫ ላይ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ሲሆን÷ ከዚህ በተጨማሪም በዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ ላይ እስከ መጨረሻው ምዕራፍ መጓዝ መቻሉ አይዘነጋም።

አሰልጣኝ ፍሬው ሉሲዎቹን በሴካፋ ሴቶች ውድድር ላይ ውጤታማ እንዲያደርጉ በእግር ኳስ ፌደሬሽን ሃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑም ተመላክቷል

ከግንቦት 14 እስከ 28 ድረስ ለ14 ቀናት በሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን ÷ ሉሲዎቹም በምድብ ሁለት ከታንዛኒያ፣ ዛንዚባር እና ደቡብ ሱዳን ጋር መደልደላቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.