Fana: At a Speed of Life!

በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ የውጪ ሃገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በብርበራው ከ71 ሺህ ብር በላይ የኢትዮጵያ ብር መያዙንም ነው ያስታወቀው።

ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንዶሚኒየም ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ወለል ፎቅ ተከራይቶ የሚኖር መሆኑን ገልጿል።

 

ተጠርጣሪው ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን እየተቀበለ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ከህብረተሰቡ ጥቆማ ማግኘቱንም ነው የገለጸው።

ጥቆማውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቀናጅተው ባደረጉት ክትትል ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ በመኝታ ክፍል ውስጥ የተገኘ 5 ሺህ 335 የአሜሪካ ዶላር፣ 380 ዩሮ፣ 1 ሺህ 435 የቻይና የን እና ሌሎች የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን ጨምሮ 71 ሺህ 635 የኢትዮጵያ ብር መያዙን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.