የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 156 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Feven Bishaw

May 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 156 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 157 ሴቶች ሁለት ሕጻናትና 995 ወንዶች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ዛሬ ከየመን በተደረገ በረራ 150 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ22 ሺህ 600 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡