Fana: At a Speed of Life!

የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ ሊፈጸም የነበረን ጥፋት አከሸፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ሃይማኖትን ከለላ በማድረግ ሊፈፀም የነበረን ጥፋት ከከተማው የጸጥታና አስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት ማክሸፋቸው ተገልጿል፡፡
 
የአጋሮ ከተማ ከንቲባ አቶ ነዚፍ መሐመድ አሚን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥በህቡዕ የተደራጁ ግለሰቦች በሃይማኖት ስም ጥፋት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በሕዝብ እና በከተማው የፀጥታ ሃይል ርብርብ ተመክረውና ተገስፀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተደርግዋል።
 
የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር በበኩላቸው፥አጋሮን ከጥፋት ተከላክለው ሰላሟን ያስጠበቁ ሁሉ ለሌሎች አካባቢዎች ሀሉ ተምሳሌት በመሆናቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
በሁሴን ከማል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.