Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለጥናት ዲዛይንና ለመስኖ መዋቅር ድጋፍ እንዲያደርግ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለጥናት ዲዛይን ለግንባታ እና ለመስኖ መዋቅር አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርግ የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ጠየቁ፡፡
ሚኒስትሯ በዓለም ባንክ የአፍሪካ ግሎባል ውኃ ትግበራ ኃላፊ ሶማ ጎህሽ ሞውሊክ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን÷ በውይይታቸውም ስለ መስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር አደረጃጀትና የወደፊት ዕቅድ፣ ራዕይና ስትራቴጂን በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡
ባንኩ ለተቋሙ በሰው ሀብት ሥልጠና፣ ለሥራ ተቋራጮችና ለአማካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ለአሰራር መመሪያና ስታንዳርድ ዝግጅት ዕገዛ እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡
ተቋሙ የተቋቋመው በቅርብ ጊዜ መሆኑን እና ከዓለም ባንክ የሚፈልገው ድጋፍ መኖሩን መገንዘባቸውን የገለጹት ሶማ ጎህሽ ሞውሊክ÷ ከሚኒስቴሩ ጋር አብረው ለመሥራትና ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም አስፈላጊውን ጥናት የሚያደርግ የቴክኒክ ቡድን ወደ ተቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚልኩ መሆኑን መግለጻቸውን ከመስኖ እና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.