Fana: At a Speed of Life!

የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን በማስቀጠል አንዳችን ላንዳችን ደጀን መሆን ይገባናል- አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆየውን የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን በማስቀጠል አንዳችን ላንዳችን ደጀን መሆን ይገባናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡
አቶ ጃንጥራር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር በመገኘት የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ ተግባር ባስጀመሩበት ወቅት÷ የቆየውን የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን በማስቀጠል አንዳችን ላንዳችን ደጀን መሆን ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ በበኩላቸው÷ የቤት እድሳት ሥራችን በቀጣዩ ሁለት ወራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.