Fana: At a Speed of Life!

በደደር ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ደደር ከተማ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የዞኑ ፖሊስ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለግንቦት 6 አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ በደደር ከተማ የገበያ ስፍራ በተነሳ የእሳት አደጋ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
በአደጋው የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥና የሕንፃ መሳሪያ መደብሮች ጉዳት እንደደረሰባቸው ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል፡፡
ህብረተሰቡ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ወደ ሌሎች ሱቆችና አካባቢዎች ሳይዛመት እና ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ዛሬ ጠዋት 12፡30 አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡
እሳቱ የተነሳበትን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.