Fana: At a Speed of Life!

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን የሀገሪቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያንን የሚተኩ ይሆናል ሲል ኤምሬትስ ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በሼክ መሀመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም የአመራር ዘመን ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሆነው አገልግለዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ73 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡
ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን አባታቸውን ሼክ ዛይድ አል ናህያንን ተክተው በፈረንጆቹ 2004 ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.