የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ የኮንትሮባንድ ንግድን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከጸጥታ አካላት ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

May 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከፌደራልና ከክልል ፀጥታ ሃይሎች አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሶማሌ ክልል የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ ንግድ መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የክልሉን አጠቃላይ ሰላም እና ደህንነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡