Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው መርሃ ግብር ለተሸላሚቹ የክብር ዶክትሬቱን አበርክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ላገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የክብር ዶክትሬቱ ሃላፊዎቹ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚው እና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ የተበረከተ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ዶክተር አኪንውሚ አዴሲና በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በልማትና ሌሎችም ተግባራት የላቀ ሚና የተወጡ ናቸው።
የአፍሪካ ልማት ባንክ 8ኛው ፕሬዚዳንት በመሆን እየመሩ ያሉት አዴሲና በአህጉሪቷ የድህነት ቅናሳ፣ የትምህርት መስፋፋት፣ የስራ ፈጠራ እና ሌሎችም ተግባራት ላይ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸው ይታወቃል።
በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ÷ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲቪል ስራዎች ግንባታ ስኬታማነት ሃላፊነታቸውን በብቃት የተወጡ ናቸው።
በግድቡ ግንባታ ስኬት የላቀ ሚና ለነበራቸው ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.