የሀገር ውስጥ ዜና

የትራፊክ አደጋ አራት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችን ህይወት ቀጠፈ

By Meseret Awoke

May 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች የነበሩ አራት ባለሙያዎች በመኪና አደጋ ህይዎታቸው አለፈ፡፡

ሰራተኞቹ በአማራ ክልል ደባረቅ ዞን ሳንቃ በር አከባቢ ልዩ ስሙ አበርጊና በሚባል ስፍራ ለመስክ ስራ ሲንቀሳቀሱ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ነው ሕይወታቸው ያለፈው፡፡

ይህንን ተከትሎም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ሃዘናቸውን ገልጸው ፥ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡