Fana: At a Speed of Life!

የአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ በእንጅባራ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ በእንጅባራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

“የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለዘላቂ ሠላም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ÷ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ ዓለምነሽ ይባስ ተገኝተዋል፡፡

በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የልዩ ኅይል እና የተለያዩ የጸጥታ ተቋማት አዛዦች እና የመንግሥ የሥራ ኅላፊዎች እየተሳተፉ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ መድረኩ የሁለቱን ክልል ሕዝብ የቆየ ትስስር እና አብሮነት የሚያንጸባርቁ የአማራ፣ አገው፣ የሽናሻ እና ጉሙዝ ሕዝቦች የተለያዩ የጥበብ ሥራዎች እየቀረቡ ነው፡፡

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ በሁለቱ ክልሎች መካከል መልካም ግንኙነትን በመገንባት በጋራ ለመሥራት፣ ለማደግ እና በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያግዛል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.