Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በባህርዳር የተገነቡና በሥራ ላይ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በባህርዳር ከተማ የሚገኙ በሃገር ውስጥና በውጭ ባለሀብቶች የተገነቡና በሥራ ላይ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን ጎብኝተዋል።

የተጎበኙት ኢንቨስትመንቶች በአግሮ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የባህር ዳር ፍሬሽ ብሉቨሪ ኢንቨስትመንት፣ የባዮ ፍሬሽ የአበባ ምርት እና በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተገንብተው ሙሉ በሙሉ ማምረት የጀመሩትን አፍሪካ ብረታ ብረት ፋብሪካና ሙሌ ዘመናዊ የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያና አማር የሲሚንቶ ከረጢት ማምረቻ ፋብሪካዎች ናቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው ማጠቃለያ ፥ የክልሉ መንግሥት ኢንቨስትመንትን በማስፋፋትና ባለሀብቶችን በመሳብ የክልሉን እምቅ ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋልና ለብዙ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ድህነትን ለማስወገድ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም ፥ ‘’ባለሀብቶቻችን የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታትና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ ነው’’ ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.