Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና አመራሮች የማዕድን ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ተመለከቱ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የማዕድን ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ተመልክተዋል።

ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹና አመራሮቹ በሚኒስቴሩ የሚገኘውን የማዕድን ጋለሪ መመልከታቸውን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ የስራ ሃላፊዎቹ በተቋሙ ለነበራቸው ቆይታና ለሰጡት ገንቢ አስተያየት ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.