የሀገር ውስጥ ዜና

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና አመራሮች የማዕድን ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ተመለከቱ

By Feven Bishaw

May 15, 2022

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የማዕድን ሚኒስቴርን የሪፎርም ስራዎች ተመልክተዋል።

ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹና አመራሮቹ በሚኒስቴሩ የሚገኘውን የማዕድን ጋለሪ መመልከታቸውን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።