Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት ለክልሉ አርሶ አደሮች ከምርት እስከ ገበያ ትስስር ያመቻቻል -አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ፋፈን ዞን ደጋህሌ ከተማ በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ዜጎች ለገበያ ያቀረቡትን ፍራፍሬ ጎብኝተዋል።

የደጋህሌ ከተማ ለግብርና ምቹ ከሆኑ የክልሉ ከተሞች አንዷ ስትሆን አርሶ አደሮች የሚያመርቱትን ፍራፍሬ ለአካባቢው በተለይ ለጅግጅጋ ከተማ ገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድም በጉብኝታቸው ወቅት አርሶ አደሮቹን አበረታተዋል።

የክልሉ መንግሥት ለግብርና ልማት ልዩ ትኩረት እንደሰጠ እና በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አርሶአደሮችም ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት አርሶአደሮቹ የዚህ አካል እንደሆኑ ገልፀው መንግሥት ከምርት እስከ ገበያ ትስስር ያለውን እንደሚያመቻች ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥት በ2015 የምርት ዘመን ከ20 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.