Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ  በኢሲኤ  መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

 

የጉባኤው ዋና አላማ የተሻሻለውን የመተዳደሪያ ደንብ ለማጽደቅ እንደሆነ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ተናግረዋል፡፡

 

ጉባኤው የተሻሻለው የፌዴሬሽኑ የመተዳደሪያ ደንብ  በጉባኤው ተሳታፊዎች በአብላጫ ድምጽ ካጸደቀ በኋላ የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንብ  ረቂቅ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበት በአብላጫ ድምጽ  መጽደቁ  ተጠቁሟል፡፡

 

የምርጫ አስፈጻሚ አካላትን ለመሰየም ምርጫ ሲካሄድ ከቀረቡት እጩዎች በተጨማሪ በተሳታፊዎች ጥቆማ ተጨምሮበት በአጠቃላይ 11 ምርጫ አስፈጻሚ እና 5 ይግባኝ ሰሚ እጩዎች ቀርበው ምርጫ መከናወኑን  ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.