Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ ፋርማጆን ጨምሮ 39 ሰዎች በእጩነት ቀርበዋል።

የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋውዚያ የሱፍ ሀጂ አደም ብቸኛዋ ሴት እጩ ሆነው ቀርበዋል።

ከምርጫው ጋር ተያይዞ ካለው የፀጥታ ስጋት አኳያ በመዲናዋ ሞቃዲሾ እስከ ነገ ማለዳ 12 ሰዓት ድረስ የትራፊክ እና ሰዎች እንቅስቃሴ ክልከላ መጣሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ከደህንነት ስጋቱ ጋር በተያያዘም ምርጫው በሀንጋር አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ነው እየተካሄደ ያለው።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ለሁለት አመታት መራዘሙ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.