Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 26 ኢንዱስትሪዎች ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው ወደ ስራ መግባታቸውን የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለጸ፡፡

የመምሪያው የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ፕሮሞሽን ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ይመር እንደገለጹት፥ በከተማው በክልል እና በፌደራል ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም በባንኮችና በመሠረተ ልማት አቅራቢዎች ድጋፍ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡

ከእነዚህ መካከል 10 የሚሆኑት ኢንዱስትሪዎች ከክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክክር ጉባኤ በኋላ ወደስራ የገቡ ናቸው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬን በጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ እንዲሁም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ 19 ሚሊየን 806 ሺህ 957 ከ80 ዶላር ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል።

ከዚህ ውስጥ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ከኢንዱስትሪ መንደር ውጭ በምርት ላይ የሚገኙት አምስት የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎች 8 ሚሊየን 698 ሺህ 27 ከ54 የአሜሪካ ዶላር ማስገኘታቸውን ገልጸዋል።

በግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በምርት ላይ የሚገኙ አምስት ድርጅቶች 11 ሚሊየን 108 ሺህ 930 ከ26 የአሜሪካ ዶላር አስገኝተዋል ነው ያሉት።

 

በአለባቸው አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.