ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጡ

By Mekoya Hailemariam

May 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

ትናንት በተካሄደው ምርጫ የመጨረሻ ድምፅ አሰጣጥ ሞሀመድ ስልጣን ላይ የነበሩትን መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆን አሸንፈዋል።

በምርጫው ሞሀመድ 214 ድምፅ ሲያገኙ ፋርማጆ 110 ድምፅ አግኝተዋል።

ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በድጋሚ ሲሆን ወደ ስልጣን የመጡት፥ በአውሮፓውያኑ ከ2012 እስከ 2017 ድረስ ሀገሪቱን በፕሬዚዳንትነት መርተዋል።