Fana: At a Speed of Life!

5ኛው የአፍሪካ አቪዬሽን ጉባኤ እና ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የአፍሪካ አቪዬሽን ጉባኤ እና ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

ጉባኤው “ለአፍሪካ ኢቪዬሽን ኢንዱስትሪ ምቹ ሁኔታን መፍጠር” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኩባንያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በዚህ መሰረት የአፍሪካ አየር መንገድ መሪዎች፣ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት እና በአቪዬሽን ንግድ የተሰማሩ አካላት እና ደጋፊ ኢንዱስትሪዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤው በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአቪዬሽን ዘርፍ እንዴት ማስቀጠል እንደሚቻል እና የኢንዱስትሪውን ዓለም አቀፍ ዓላማ ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ይደረጋል።

ለአምስተኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ይህን ጉባኤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል።

የአፍሪካ አቪዬሽን በቻይና ውሃን ከተማ መነሻውን ያደረገው የኮሮና ቫይረስ በስሩ የሚገኙ ደንበኞቹን እና ሰራተኞቹን እንዳያጠቃ በቅርበት ክትትል እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.