Fana: At a Speed of Life!

ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መድሃኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋሟት ጋር በጋራ በመሆን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መድሃኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በአሶሳ ከተማ ተገኝተው ማስረከባቸውን የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፉ በተለይም በጸጥታ ምክንያት በጤናው ዘርፍ የደረሰውን የመድሃኒት እጥረት ለመቅረፍ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.