Fana: At a Speed of Life!

የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንሰራለን – የፌዴሬሽን ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንደሚሰራ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡
ምክር ቤቱ ከሁሉም ክልልና የሁለቱም ከተማ አስተዳደር የፍትህ አካላት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ባስተላለፉት መልዕክት፥ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት፣ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን፣ በዜጎች ዘንድ የሕገ መንግሥትና ፌዴራሊዝም እሳቤዎች እንዲሰርፁ፣ በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች መካከል የሚከፋፈለው የጋራ ገቢዎች እና የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠው ድጎማ የሚከፋፈልበት ቀመር ይበልጥ ፍትሓዊ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግስታዊ መብቶችና ጥቅሞች እንዲረጋገጡ፣ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር በማድረግ በኩልም አበረታች ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚወከሉበት ቤት መሆኑን የጠቀሱት አፈጉባኤው ምክር ቤቱ የሕገ መንግስቱ ጠባቂ የሆነ ሕገ መንግስታዊ ተቋም እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
የመድረኩ አላማ በሕገ መንግስት ትርጉም ላይ ግንዛቤ ማሳደግ እንደሆነ መገለጹን ከፌዴሬሽን ምክርቤቱ ያገኘነው ረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.