ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት የሕብረቱ ኮሚሽን በጠራው ስብሰባ ላይ ተሳተፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በጠራው የበይነ መረብ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ተሳትፈዋል።
ስብሰባው የአፍሪካ የክትባት ምርት የዓለም አቀፍ የገበያና የሥርጭት መድረኮች ውስጥ መግባት ስለሚችልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በስብሰባው የሩሲያና የዩክሪን ጦርነት በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ እያመጣ ስላለው ቀውስ አህጉራዊ መፍትሄ ማበጀት እንደሚያስፈልግ የሀገራት መሪዎች ተናግረዋል።
በስብሰባው ላይ የተጋበዙት አገራት ክትባት ለማምረት አቅም ያላቸው እና አቅም እየገነቡ ያሉ አገራት መሪዎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንትና የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በመድረኩ በእንግድነት መሳተፋቸውን ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።