በደቡብ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቋል፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የኢንቨስትመንትና ዳያስፖራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደምሰው ባቾሬ እንደተናገሩት ፈቃዱ የተሰጠው በግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፎች የኢንቨስትመንት መመዘኛ ላሟሉ 244 ባለሃብቶች ነው።
ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሃብቶች ወደ ስራ እንደገቡ መግለጻቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ፕሮጀክቶቹ በሙሉ አቅም ማምረትና አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ለ7 ሺህ 466 ዜጎች ቋሚ እንዲሁም ለ14 ሺህ 977 ጊዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል።