የኢትዮጵያና ፖርቹጋልን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክረ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊሳ ፋርጎሶ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ምክክር አድርገዋል።
በሁለቱም በኩል የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ለፖርቹጋል ባለሀብቶች በማስተዋወቅ የፖርቹጋልን ኢንቨስትመንት ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ ስምምነት ላይ መደረሱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።