የሀገር ውስጥ ዜና

በሰቆጣ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ ተደረገ

By Feven Bishaw

May 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ “ኢስተርን ኬፕ ኡምታታ ከተማ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባ አማራ ወጣቶች ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን በሰቆጣ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ዘነበ በለጠ ÷ በደቡብ አፍሪካ “ኢስተርን ኬፕ ኡምታታ” ከተማ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የስንዴ ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸው ተናግረዋል፡፡