በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋርን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ24ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሰዓት በኋላ በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጅማ አባ ጅፋርን አሸንፏል፡፡
ጨዋታውን ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ÷ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ጋቶች ፓኖም በቅጣት ምት በ57ኛ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ረፋድ ላይ በተደረገ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
በደረጃ ሠንጠረዡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ54 ነጥብ መሪነቱን ሲይዝ÷ ፋሲል ከ ነማ በ43 ነጥብ ይከተላል፡፡