Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ታሪክ እና ባህል ምሁሩ አቶ ስንታየሁ ቶላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ታሪክ እና ባህል ምሁሩ አቶ ስንታየሁ ቶላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
አቶ ስንታየሁ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የኦሮሚያ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
አቶ ስንታየሁ በኦሮሚያ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ከባለሙያ እስከ ምክትል የቢሮ ሃላፊነት በመሆን የኦሮሞ ህዝብን ባህል በአገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
ህይወታቸው እስከሚያልፍ ድረስም በኦሮሞ ምርምር እና ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር፡፡
የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የማይደሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ በነበረው ሒደት ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም ተነግሯል፡፡
አቶ ስንታየሁ የኦሮሞ ባህልና ታሪክ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ የቆዩ የዘርፉ ምሁር መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
አቶ ስንታየሁ ቶላ የሁለት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.