Fana: At a Speed of Life!

ኤልሳቤት ቦርን የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤልሳቤት ቦርን በ30 አመታት ውስጥ የመጀመሪየዋ የፈረንሳይ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተሾመዋል፡፡
በሀገሪቱ የሰራተኛ ሚኒስትር የነበሩት ኤልሳቤት ቦርን÷ የ61 አመቱን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዣን ካስቴክስን ተክተው የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል፡፡
ተሰናባቹ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዣን ካስቴክስ የፕሬዚዳንት ማክሮን ዳግም መመረጥን ተከትሎ ለአዲሱ መንግስት የለውጥ አካል ለመሆን በሚል ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦርን ከስነምህዳር ፣ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከዴሞክራሲ እና ከደህንነት ጋር በተያያዘ ከአዲሱ የሀገሪቱ አስተዳደር ጋር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የቦርን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾም በአብዛኛዎቹ የመንግስት ደጋፊዎች ድጋፍ የተቸረው ሲሆን በተፎካካሪ ፓርቲዎች በኩል ግን ተቃውሞ ማስተናገዱ ታውቋል ፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.