የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ341 ሚሊየን በላይ ችግኝ አዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ341 ሚሊየን በላይ ችግኝ ማዘጋጀቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው÷ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩን በኮንታ ዞን አስጀምረዋል፡፡
አቶ ማስረሻ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ በክልሉ በተጀመረው የክረምት ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከ341 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ከተዘጋጀው ችግኝ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
በፍሬው አለማየሁ