Fana: At a Speed of Life!

በሞዛምቢክ ከእስር እንዲፈቱ የተደረጉ 32 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞዛምቢክ በእስር ላይ የነበሩ 32 ኢትዮጵያውንን በማስፈታት በሰላም ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
ኤምባሲው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ሥራዎችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን እና በዚህም በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ምክንያት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓጓዙ በሞዛምቢክ የጸጥታ አካላት ለእስር የተዳረጉ 32 ኢትዮጵያውያንን ከሚመለከታቸው የአገሪቱ የመንግስት አካላት እና በሞዛምቢክ ዓለምቀአፉ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመነጋጋር ማስፈታቱን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም በዚምባቡዌ፣ በዛምቢያ እንዲሁም በናሚቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለማስፈታት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እና የዓለምቀፉ የፍልሰት ድርጅት ጋር የቅድመ ማጣራትና የጉዞ ሰነድ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ  መሆኑንም ነው ኤምባሲው ያሳወቀው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.