ስፓርት

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ አበባ ከተማና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

By Meseret Awoke

May 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ24ኛ ሳምነት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ አበባ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ረፋድ 4 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ሪችሞንድ አዶንጎ ለአዲስ አበባ ከተማ ጎል ሲያስቆጥር ፥ ሄኖክ አየለ ለድሬዳዋ ከተማ ባለቀ ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ቡድኖቹ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ከተማ ነጥቡን 24 በማድረስ ባለበት 14ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፥ ድሬዳዋ በ28 ነጥብ 2 ደረጃዎችን አሻሽሎ 10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡