Fana: At a Speed of Life!

የፑንት ላንድ የልዑካን ቡድን በሶማሌ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አተገባበርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፑንት ላንድ የልዑካን ቡድን አባላት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በጎልጄኖ ወረዳ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ።

በሶማሌ ክልል በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አተገባበር ልምድ እየወሰዱ የሚገኙት የፑንት ላንድ የአካባቢ ጥበቃና የገጠር መሬት አስተዳደር ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ፥ ከክልሉና ከፌደራል የፕሮጀክቱ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በፋፈን ዞን ጎለልጄኖ ወረዳ ቆህሌ ቀበሌ በፕሮጀክቱ የተተገበሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በዓለም ባንክ የሚደገፈው የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ተግባራዊ ከተደረገባቸው የክልሉ ወረዳዎች መካከል የጎልጄኖ ወረዳ አንዱ ነው።

የፑንት ላንድ ልዑካን ቡድን አባላት ፥ በወረዳው ቆህሌ ቀበሌ የመሬት መራቆትን ለመከላከልና የግጦሽ ልማትን ለማሳደግ ተግባራዊ የተደረገ የአፈርና የውሀ ጥበቃ ፕሮጀክትን ተመልክተዋል።

በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ በጅግጅጋ ከተማ ካራማራ ተራራ አቅራቢያ የተሰራ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራዎችን ተመልክቷል።

ከፑንት ላንድ የመጡ የአካባቢ ጥበቃና የገጠር መሬት አስተዳደር ባለሙያዎቹ ፥ በክልሉ ቆይታቸው በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ጠቃሚ ልምድ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

የቆላማ አከባቢዎች የኑሮ ማሻሺያ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል 36 ወረዳዎች ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ፥ የህብረተሰቡን ህይወት የሚያሻሽሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.