Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለአንድ ዓመት የሚቆይ በሠላም ግንባታ፣ በአብሮነት እሴት እና በእርቀ ሠላም እንዲሁም በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቅ ዙሪያ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በመተባበር ነው የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት የተፈራረመው፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ በባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው እና በጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን (ቀሲስ) ታጋይ ታደለ መካከል የፊርማ ሥነ ሥርዓት መከናወኑን ከጉባዔው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.