Fana: At a Speed of Life!

በ500 ሚሊየን ብር በወረኢሉ ከተማ ለሚገነባው የግብርና ምርምር ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት በ500 ሚሊየን ብር 23ኛውን የግብርና ምርምር ማዕከል በአማራ ክልል ወረኢሉ ከተማ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን እንደገለጹት የማዕከሉን ግንባታ በማዘመን የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን ይሰራል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ችሎት ይርጋ በበኩላቸው÷ የግብርና ልማቱን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር እና ለማላመድ የምርምር ማዕከላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ግንባታው ፍጥነት እና ጥራትን መሰረት አድርጎ በአምስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመላክተዋል፡፡
በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ÷ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለሚደረገው ሽግግር የምርምር ማዕከሉ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.