Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የዕርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የፈረንሳይ መንግስታት የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የዕርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የገንዘብ ድጋፉ የፈረንሳይ መንግስት በኢትየዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ ሶስት የተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመጀመሪያው ፕሮጀክት÷ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ጥገና እና ክብካቤ ስራ ሲሆን፥ ቅርሶቹ ለጎብኚ ምቹና ሳቢ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ሁለተኛው ፕሮጀክት ደግሞ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያስገነባውን የስልጠና ተቋም ግንባታና የውስጥ መገልገያ መሳሪያዎች የማሟላት ስራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሦስተኛው፥ በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ኤጀንሲ ድጋፍ ነው ተብሏል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ልማት ድርጅት ኃላፊ ቫሌሪ ቲአዎ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ በተገኙበት ተፈርሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.