በርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ልዑክ በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ልዑክ በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኘ፡፡
የክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተካሄደው አገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ መጠናቀቁን ተከትሎ በክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ልኡክ በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትዎችን የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል።
በዚህም ” ኃይሌ አዲስ ” የጥጥ ማዳመጫ ፋብሪካና ” ጉር ” የዱቄት ፋብሪካ የጉብኝቱ አካል ነበሩ።
በጉብኝቱ የክልል ፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ የአምራች ኢንዱስትሪ ተወካዮችና የሥራ ባለድርሻ አካላትም መገኘታቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡