Fana: At a Speed of Life!

በባቲ የህወሓት ወራሪ ሀይል ጥሎት የሄደው ፈንጅ ባለማወቅ ሲነካካ በመፈንዳቱ ህፃናትን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባቲ ከተማ አንድ ግለሰብ የህወሓት ወራሪ ጥሎት የሄደውን ፈንጅ ባለማወቅ ሲነካካ በመፈንዳቱ የራሱና የሦስት ህፃናት ህይወት አለፈ።

በዛሬው ዕለት በግምት ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 አካባቢ ሲሆን፥ በባቲ ከተማ በ03 ቀበሌ በተለምዶ አዲሱ ሰፈር የህወሓት ወራሪ ሀይል ጥሎት የሄደውን ፈንጅ አንድ ግለሰብ ባለማወቅ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሲነካካ በመፈንዳቱ የራሱንና ሦስት ህፃናት ህይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ ገለጸ፡፡

በተጨማሪም በሁለት ሴቶች እና በሦስት ህፃናት ላይ በድምሩ በአምስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.