Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያና ሶማሊያ የሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር እንደሚሰሩ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያና ሶማሊያ የሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር እንደሚሰሩ ተመራጩ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ገለፁ።

ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ገፃቸው ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫ ባስተላለፉት የምስጋና መልዕክት፥ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ባለፈው እሁድ የሶማሊያ ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ከፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋር ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ በሆኑ ሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው በጋራ እንደሚሰሩም እምነታቸውን ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.