Fana: At a Speed of Life!

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት በተለያዩ ክልሎች መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠት ተጀመረ።
ክትባቱን በአፋር ክልል ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሀቢብ እንደገለጹት፥ ክትባቱ በክልሉ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ይካሄዳል፡፡
ክትባቱ ከ400 በላይ በሚደርሱ ጣቢያዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 14 ቀን ድረስ ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡
ክትባቱ ከ6 ወር እስከ ሁለት ዓመት እድሜ ላላቸው ከ200 ሺህ በላይ ሕጻናት ተደራሽ እንደሚሆን ገልጸው ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ተጀምሯል።
ለዘመቻው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የክልሉ ጤና ቢሮ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በዘመቻው ዕድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት ድረስ የሆናቸው 45 ሺህ 695 ያህል ሕጻናት እንደሚከተቡ እና ለዚህም 968 ከታቢዎች መመደባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመሀመድ አሊ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.