Fana: At a Speed of Life!

የሰላምና የፀጥታ ተቋማት የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ግንቦት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሰላምና የፀጥታ ተቋማት የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በምክክር መድረኩ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለምና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የዘጠኝ ወር ሪፖርት አቅርበው ወይይት የሚደረግበት ሲሆን አገር አቀፍ የግጭት አዝማሚያን የሚመለከት የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተስፋዬ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.