በአማራ ሊግ እየተወዳደሩ ለሚገኙ ክለቦች የኳስ ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአማራ እግር ኳስ ሊግ እየተወዳደሩ ለሚገኙ ክለቦች የኳስ ድጋፍ አደረገ፡፡
በአራት ምድብ ተከፍሎ እየተከናወነ የሚገኘው የአማራ ክልል ሊግ የምድብ አንድ ውድድር በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ተሳታፊ ለሆኑ ክለቦች ኳስ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ተፈሪ ካሣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው አስረክበዋል።
አቶ ኢሳያስ ከዚህ ቀደም በአማራ ሊግ ምድብ ሐ ውድድር መክፈቻ ወቅት በደባርቅ ከተማ ተገኝተው ተመሳሳይ የኳስ ድጋፍ ማስረከባቸውን የፌዴሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡