አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች 970 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ እንደገለፁት÷የዘንድሮው የበልግ ዝናብ ዘግይቶ ቢጀምርም ቀድሞ የእርሻ ማሳ ዝግጅት በመደረጉና 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የፋብሪካ ማዳበሪያን ጨምሮ የምርጥ ዘር አቅርቦት አርሶ አደሩ እጅ እንዲደርስ በመደረጉ ውጤታማ መሆን መቻሉን ተናግረዋል።