አዳማ ከተማ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር በስምምነት ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ያለፉትን አስር ጨዋታዎች በሊጉ ማሸነፍ ያልቻለው አዳማ ከተማ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር በስምምነት ተለያየ፡፡
የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከመጀመሩ በፊት አዳማ ከተማን ለማሰልጠን ፊርማውን ያኖረው አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ÷ በዝውውር መስኮቱ ራሱን በማጠናከር ውድድር ቢጀምርም እስካሁን ከአራት ጨዋታዎች በላይ ቡድኑን ለድል ማብቃት አለመቻሉ ተገልጿል፡፡
የፋሲል ምክትል የነበሩት ይታገሱ እንዳለ በቀሪ የሊጉ ጨዋታዎች ቡድኑን በጊዜያዊነት እያሰለጠኑ እንዲቀጥሉእንዲቀጥሉ ክለቡ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
አዳማ ቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብሩን በሳምንቱ መጨረሻ በደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ከሚገኘው ሰበታ ከተማ የሚያደርግ ይሆናል።