Fana: At a Speed of Life!

በአበርገሌ ወረዳ በአሸባሪው ህወሓት ቁጥጥር ስር በሚገኙ 12 ቀበሌዎች በተቀሰቀሰ ወረርሽኝ ህፃናት ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አበርገሌ ወረዳ አሸባሪው ህወሓት በወረራ በያዛቸው 12 ቀበሌዎች ውስጥ በተቀሰቀሰ ወረርሽኝ ህፃናት ለሞት እየተዳረጉ በመሆኑ መንግስት ከዓለም አቀፍ ድንበር የለሽ የህክምና ተቋማት ጋር በመነጋገር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ በዞኑ በሚገኘው አበርገሌ ወረዳ አሸባሪው ህወሓት በያዘባቸው 12 ቀበሌዎች ዓይነቱ በውል ያልታወቀ አዲስ ወረርሽኝ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ወረርሽኝም እስካሁን የዘጠኝ ህጻናት ህይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡

አሁን ላይ አካባቢዎቹ በአሸባሪው ህወሓት ቡድን በቁጥጥር ስር ከመሆናቸው ጋር ተያይዞም ለዜጎች አስፈላጊውን የጤና ባለሙያ እገዛ መስጠት አለመቻሉንም ዞኑ አመልክቷል፡፡

ስለሆነም መንግስት በአካባቢው የሚገኙ ዜጎችን ከወረሽኙ ለመታደግ አስቸኳይ የምግብና የመድሐኒት እርዳታ የሚደርስበትን ሁኔታ በፍጥነት እንዲመቻች ከዓለም አቀፍ ድንበር የለሽ የህክምና ተቋማት ጋር በመነጋገር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን ሲል መምሪያው ጠይቋል፡፡

የአብርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ክፍሌ ወረርሽኙ በዚህ ሳምንት ግንቦት 7 ቀን የተከሰተ መሆኑን ጠቁመው ÷ ከህጻናት ባሻገር አዛውንቶችም እየተያዙ እንደሆነ መናገራቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነውመረጃ ያመላክታል፡፡

አበርገሌ ወረዳ እስካሁን ከአንድ ዓመት ስድስት ወር ገደማ በጠላት ስር መሆኗን የገለጹት አስተዳዳሪው÷ እስካሁን በአካባቢው በረሃብ፣ በእርዛትና በበሽታ ምክንያትከ 120 ሰው በላይ ዜጎች ህይወት ማለፉን ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.