Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የ40 አቅመ ደካሞች ቤትን አፍርሶ እንደ አዲስ የመገንባት መርሐ ግብርን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ40 አቅመ ደካሞች ቤትን አፍርሶ እንደ አዲስ የመገንባት መርሐ ግብርን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስጀምረዋል።
ከንቲባ አዳነች በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ወረዳ 10 ጨርቆስ አካባቢ እጅግ በተጎሳቆለ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ቤቶችን ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ መልሶ በአዲስ መልኩ የመገንባት ስራን ነው ያስጀመሩት።
ሄይኒከን ቢራ ፋብሪካ ቤቶቹን የመገንባት ስራን እንደሚያከናውን ተገልጿል።
ግንባታው በ15 ሚሊዮን ብር የሚከናወን ሲሆን፥ በሁለት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡

 

ከንቲባ አዳነች አበቤ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ዜጎቹ ያሉበት ሁኔታ ምቹ አለመሆኑን ገልፀው፥ የልማት አጋር በማፈላለግ መልሶ ለመገንባት መሰራቱን ተናግረዋል።
“በተገባው ቃል መሰረትም ቤቱን አጠናቀን እናስረክባችኋለን” ብለዋል።
ከተማዋ የምትለማው በመንግስት ብቻ ሳይሆን ኃላፊነታቸውን በሚወጡ ተቋማት አብሮ መስራት ነውም ብለዋል።
ይሄው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.