ሚኒስቴሩ ባለፉት አስር ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የገቢዎች ሚኒስቴርን እና የተጠሪ ተቋማቱን የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያዳመጠ ነው፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ባቀረቡትሪፖርት፥ ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ 360 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ባለፉት አስር ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥም 168 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ከአገር ውስጥ ገቢ ታክስ የተገኘ ሲሆን፥ 113 ነጥብ 8 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተገኘ ገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የአቅዱን 93 ነጥብ 1 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው አቶ ላቀ በሪፖርታቸው ያመላከቱት፡፡
በመላኩ ገድፍ